August 25, 2026
ዜና (News)
6
የስራ ኃላፊዎች አቀባበል እና ትውውቅ ተደረገ።
የስራ ኃላፊዎች አቀባበል እና ትውውቅ ተደረገ።
የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ እና የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች አቀባበል ትውውቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ በታላቅ መንፈሳዊ ደስታና ድምቀት ተከናወነ።
በዚህ መርሐግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የሸገር አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ ክቡራን እንግዶች በስፍራው ተገኝተዋል።