June 17, 2026 ዜና (News)
  • 23
  • ††† እንኳን  ለሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወርሐዊ  በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

    ††† እንኳን  ለሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወርሐዊ  በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

    ††† ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ †††

    አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ነው::

    👉 እናት ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን እንዲ ብላ ትጠራዋለች  ።

    ¤ ወንጌላዊ
    ¤ ሐዋርያ
    ¤ ሰማዕት ዘእንበለ ደም
    ¤ አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
    ¤ ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
    ¤ ወልደ ነጐድጉዋድ
    ¤ ደቀ መለኮት ወምሥጢር
    ¤ ፍቁረ እግዚእ
    ¤ ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
    ¤ ቁጹረ ገጽ
    ¤ ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
    ¤ ንስር ሠራሪ
    ¤ ልዑለ ስብከት
    ¤ ምድራዊው መልዐክ
    ¤ ዓምደ ብርሃን
    ¤ ሐዋርያ ትንቢት
    ¤ ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
    ¤ ኮከበ ከዋክብት

    በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን።
    ❤63🙏22👏3👍1