July 28, 2026 ዜና (News)
  • 14
  • የሰ/ት/ቤቱ አዲሱ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት  ቃለ መሐላ ፈጸሙ።

    የሰ/ት/ቤቱ አዲሱ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት  ቃለ መሐላ ፈጸሙ።

    የደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና  መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤ/ክ የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት  አስመራጭ ኮሚቴ አዲስ የተመረጡትን የሥራ አመራር አባላትን እና የአፈጻጸም ክትትልና ቁጥጥር አባላትን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት  በቅንነት፣ በታማኝነትና በግልጽነት አገልግሎቱን እንዲፈጽሙ  ቃለ የማስገባት መርሐ ግብር  እና በአዱሱ የሰንበት ት/ቤቶች መዋቅር መሰረት የአገልግሎት ድልድል ማሳወቂያ መርሐ ግብር  በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

    በዚህም መሠረት ሥራ አመራር ጉባኤ

    1. ተስፋዬ ሞላ-------- ዋና ሰብሳቢ
    2. መኮንን ሀይሌ --------ምክትል ሰብሳቢ
    3. ሜላት መኮንን ------- ጸሐፊ
    4. ተስፋነሽ ከበደ------- ሒሳብና ንብረት አስተዳደር ማስተባበሪያ
    5. ቀሲስ ማስተዋል መኳንንት------- የትምህርትና ዕቅበተ እምነት ማስተባበሪያ
    6. ዘላለም አበበ---------- የአባላትና ተቋም አደረጃጀት ማስተባበሪያ
    7. ብሩክ ሙሉጌታ--------- እቅድ ጥናትና ምርምር ማስተባበሪያ
    8. በሀይሉ ጌታቸው------ መረጃና ወቅታዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ
    9.  በለጠ ሸንቁጤ------- ሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ
    10. ቢንያም ወንድምኩን-------ቴክኒሎጂ ትስስር ማስተባበሪያ
    11. ረድኤት ተስፋዬ------ምጣኔ ሐብትና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

    ለአፈጻጸም ክትትል እና ቁጥጥር ጉባኤ

    1. ሄኖክ ግርማ ------  ዋና ሰብሳቢ
    2. ምንተስኖት ታደሰ------ምክትል ሰብሳቢ
    3. ትዝታ አራጌ-------- ጸሐፊ
    4. ሮቤል ሚካኤል-------አባል
    5. ሮዛ መልስ-----አባል ሆነው መመደባቸው ተገልጿል

    በመጨረሻም  አዲሱ  የሰንበት ት/ቤቱ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ተስፋዬ ሞላ  ባስተላለፉት መልእክት አዲሱ ሥራ አመራር ጥሩ የአገልግሎት ጊዜ እንዲሆንለት ሁላችሁም የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በጸሎት፣ በሀሳብ ፣ አገልግሎትን ተግቶ በማገልገል እዲያግዟቸው ጥሪ አቅርበው  መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
    ❤2