July 23, 2026
ዜና (News)
19
የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ታቦተ ሕጉ ወደ ነባሩ መንበረ ክብሩ ተመለሰ።
የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ታቦተ ሕጉ ወደ ነባሩ መንበረ ክብሩ ተመለሰ።
በረጅም ዘመን አገሎግሎት ተጎድቶ የነበረው የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የእድሳት ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ተባረከ።
ከምረቃውና ቡራኬው ሥነ ሥርዓት በኋላም ታቦተ ሕጉ ጊዜያዊ
ከነበረበት መቃኞ ወጥቶ ወደ ነባሩ ቤተ መቅደስ በክብር
ገብቷል ።
በዚሁ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ የሥራ ኃላፊዎች፣ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ፣ መልአከ ኃይል አባ ሠላማ የገዳሙ አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ ሊቃውንት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንዲሁም በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተግኝተዋል።
© የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
❤2