June 17, 2026 ዜና (News)
  • 15
  • "በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን" የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

    "በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን" የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

    የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተፈጠረው የኦርቶዶክሳውያን ግድያና የቤተ ክርስቲያን መቃጠል ኃዘናቸውን ገልጸው በብፁዕነታቸውን መመሪያ ሰጪነት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳወቁ።

    አስተዳዳሪዎቹ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የጋራ ስብሰባ ለጽድቅና ለመንግሥተ ሰማይ ዓላማ የሚሰበሰብ የቤተክርስቲያን ገቢ አስመልክቶ ውይይትና ምክክር በተደረገበት ስብሰባ ላይ ነው።

    በስብሰባው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ወና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ትፍስሕት ሙሉጌታ ቸርነት የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አክኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት እእተዳዳሪዎች የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና የአድባራት የሒሳብ ሹሞች ተገኝተዋል።
    ❤3